International NewsLocal NewsNewsopinion & AnalysisOpinion and analysis

እኔ ላይ እና ሚዲያችን አምባሳደር ሚዲያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በደህንነት አካላት ተፈጸመብኝ

    መጋቢት 7 ፒያሳ አካባቢ የሚገኘው ቢሮአችንን ወደ 5 ሰአት አካባቢ ስራችንን በመስራት እያለን ሶስት የደህንነት አባላት ወደ ቢሮአችን ገቡ። ቢሮ ውስጥ ሶስት ነበርን ለነሱ ደህንነት ስል ሰማቸውን አልጠቅሰውም ወዲያው የምንሰራውን እንድናቆም እና ከዚህ ሰአት ጀምሮ በህግ ቁጥጥር ውስጥ እንደሆንኩ እና መታወቂያውን አውጥቶ አሳየኝ ከመረጃ እና ደህንነት የሚል ነበር  በመቀጠል አንደኛው ሲቪል በካቴና እጄን አጥብቆ አሰረው ከዛም ጠረጴዛ ላይ የነበሩትን ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና የግል የምንጠቀምናችውን  ስልኮች ሙሉ ወሰዱኣቸው ከኪሴ ውስጥ ቁልፎች አውጥቶ ለዜና አገልግሎት የምንጠቀምባቸውን ካሜራዎች፣የድምጽ መቅጃዎች እንዲሁም ሀርድ ዲስኮች በሙሉ መሰብሰብ ጀመሩ። 

ከዛም ሁለት አማራጭ እንዳለኝ እና በሰላም ት ሄዳለህ ወይስ ሀይል ተጠቅመን ት ሄዳለህ ምንም አማራጭ ሰለሌለኝ እጄ ላይ ካቴና እንዳሰሩ ሁለቱን የስራ ባልደረቦቼን ኣስፈራርተዋቸው ከዚህ በሁኣላ በኢህ መስሪያ ቤት ብናገኛች ሁ የእሱ እጣፋንታ እንደሚደርሳቸው እና እርምጃ እንደሚወስዱባቸው አስጠንቐዋቸው ወጡ።

   ከዛም ከነበርንበት ቢሮ ወደመጡበት መኪና ይዘውኝ ወረዱ መኪናው V8 የሚባለው መኪና ሲሆን ከውጭ ወደ ውስጥ ምንም የማያሳይ አይነት ነው እኔን ከሁኣላ ካስገቡኝ በሁኣላ መገልገያ እቃዎችን አስገቡ ከዛም ተከታትለው ገቡ ልክ እንደገቡ አይኔን በጥቁር ጨርቅ መንም እንዳይታየኝ አድርገው አሰሩት ቢያንስ ለ 1:30 በላይ የሚሆን ሰአት ተጉዝን በዝን ወቅት ወዴት እንደሚወስዱኝ እና ምን ሊያረጉኝ ነው ብዬ ለመጠየቅ ሞከርኩ  አንደኛው አባል ግን በቦክስ ሆዴን በመምታት አርፈህ ተቀመጥ በማለት እዛ ስርደርስ ታቀዋለህ በማለት ጮሀብኝ ካዝም ወዲያ የሚከተለኝ ነገር ለላ እንደሚሆን ስላወኩኝ ምንም ጥያቄ አላቀረብኩም። በጉዞው ውስጥ እርስ በእርስ በኦሮምኛ ቁንቃ ነበር የሚያወሩት የሚናገሩት ምንም ባይገናኝም በየመሀሉ ግን የፋኖ፣ሸኔ ምናምን እያወሩ ነበር የደረስነው።

  የሚወስዱኝ ቦታ እንደደርስን ከመኪና አይኔ ሳይፈታ ወደ አንድ መመርመሪያ ክፈል ወሰዱኝ ብርሀን የሌለበት  ጨለማ እና ቀዝቃዛ ክፍል ወርውረውኝ በሩን ዘግተው ወጡ። ከጥቂት ጊዜ በሁላ ሁለት ሌላ መርማሪዎች ክፍሉን ከፍተው ገቡ መጀመሪያ አይኔ ላይ የታሰረውን ጨርቅ ፈቶ ወንበር ላይ አስቀመጠኝ ። ከዛም አንደኛው መርማሪ መጠየቅ ጀመረ ስለ አንተ ሁሉም መረጃ አለን ከማን ጋር እንደምሰራ እና የት እንደምትኖር እናቃለን እነ እንደምፈልገው የማትመልስልኝ ከሆነ ካላስደሰተኝ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ትገባለህ በማለት አስፈራራኝ

      መጀመሪያ ላይ ከፋኖ ጋር እንደምትሰራ እናውቃለን የአዲ አበባ ፋኖ አባል ነህ የት ነው የምትገናኙት የት ነው የምሰበሰቡት  አማራ ክልል ካሉ ፋኖ ጋር እንዴት ነው የምትሰሩት በማለት መጠየቅ ጀመረ።እኔም  የፋኖ አባል እንዳልሆንኩ እና በዋነኝነት ሰለ አማራ ክልል ግደያ እንደምዘግብ  ከ አመራሮቹም ጋር ምንም ግንኙነት እንደለለኝ ማስረዳት ጀመርኩ። በተደጋጋሚ የፋኖ አመራሮችን ስም እየጠራ የት ነው ያሉት አውጣ እያለ መጮህ ጀመረ መርማሪው ፊቱ እየተቀየረ እየተናደደ መጣ ለሌላኛው ሰውዬ በኦሮምኝ የሆነ ነገር ብሎት ያም ሰውዬ ወዲያውኑ እግሬን አስሮ ድብደባውን ጀመረ ንትናገር ይሻሀል እያለ መደብደብ ጀመረ በጫማው እና በዱላ እግሬን እና ጀርባዬን መደብደብ ጀመረ መርማሪው በድብደባው ስዐት ብትናገር ይሻልሀል እያለ የጮህንኛል ድብደባውን ካደረሱብኝ በሁኣላ በድጋሚ በሩን ዘግተው ወጡ።

     ተመልሰው ሁለቱ መርማሪዎቹ በሩን ከፍተው ገቡ ደጋሚ ከመሬት ላይ ስቦ አንስቶኝ ወንበር ላይ አስቀመጠኝ በመቀጠል መርማሪው ቅድም የመለስክልኝ መልስ ምንም አላስደሰተኝም አሁን ለምጥይቕ ነገር አሁንም ማልፈልገውን መልስ ከመለስክ ከቅድሙበላይ ነው የሚከተልህ በማለት ማስፈራራት ጀመረ ቀጥሎም አዲስ አበባ ውስጥ ከሁለት ቀን በፊት ስለ ተከሰተው መጠየቅ ጀመረ ጥቃቱ እንደሚደርስ ቀድመህ ታውቅ ነበር ጥቃቱን ካደረሱት ጋር ግንኙነት ነበረህ በቦታው ላይም የተገኝኸው መረጃው ቀድሞ ሰላለህ ነው። በዛን ቀን ዘገባህም የመንግስትን ስም የሚያጠፋ ዘገና ነው የሰሯኸው አዛ ላይ ማነው ለህዝቡ ጠበቃ ያደረገህ ሰዎች መታሰራቸው ምን አገባህ  ነማለት መጠየቅ ጀመረ እኔም በቦታው የተገኘሁት በ አጋጣሚ እንደሆነ እና እና የዘገብኩት ያየሁትን ነው ቭንጂ ሌላ አደለም ጥቃቱን ከፈጽሙት ጋርም ምንም ግንኙነት እንደሌለኝ እና እንደማላቃቸው ማስረዳት ጀመርኩ ምንም ሊያምነኝ ፍቃደኛ አደለም የባሰውኑ እየጮኸ ማስፈራራት ጀመረ እዝው ነ ገለን የምንጥልህ፣አንተን ብሎ ጋዜጠኛ የምትጮህለት ህዝብ መቶ ያድንህ እንደሆነ እናያለን ማለት ጀመረ።መረጃ ዜናዎችን ማነው የሚያቀብልህ በዛው ላይ ተያይዞ የአምንስቲ ሪፖርት ለምን ዘገብክ ይኸ መንግስትን ለመጣል ከውጭ ጋሉ ጋዜጠኞች ጋር ያደረከው  ሙከራ ነው በማለት ድጋሚ ይጮሀል። ከዛም እንድቅድሙ ለባልደረባው ት ዛዝ ሰጥቶት በድጋሚ ከወንበሩ ላይ በእርግጫ መቶ ወደ ወለሉ ጥሎኝ ደብደባውን ቀጠለ ዋነኛ መርማሪው  በተደጋጋሚ ብትናገር ይሻልሀል ወደ ሌላ የምርመራ ክፍል ወስደው ለሰው ልጅ ላይ ሊደረግ የማይገባ ድብደባ እና በኤሌክትሪክ ቶርች ራሴን እስክስት ድረስ  ፈጸሙብኝ። በድጋሚ ስነቃ ድቅድቅ ጫካ ጨለማ  ውስጥ አስረው ማሰቃየት ጀመሩ በመጨረሻም ወደማላቀው ቦታ ባመጡኝ መኪና ተመሳሳይ ወርውረውኝ ሄዱ። 

ወደፊት ያለሁበትን ቦታ በማሳወቅ የደረሰብኝንም ነገር በዝርዝር የምዘግብላችሁ ይሆናል።

     ይህ የሚያሳየው በኢትዮጵያ ያለውን ስርአት የሚያሳይ እና ማንኛውም ሰው ሃሳቡን መግለጽ የማይችልበት ሀገር እንደሆነች ነው። በነጻነት ሀሳኑን መግለጽ የሚፈልግ ሁሉ ያስራሉ፣ ከመንግስት ተቃራኒ ሀሳብ ያላቸው ሁሉ ይገድላሉ፣ብሄር ተኮር አድርገው በየቦታው ጄኖሳይድ ይፈጽማሉ የህን አገዛዝ በውጭ ሀገር ያለንም በውስጥ ያለንም ሰዎች ታግለን ከስልጣን ማስወገድ ይኖርብናል በአሁን ሰዐት ከሀገር ወጥቼ ነው ያለሁት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በአምባሳደር ሚዲያ የተለያዩ  የዜና ማሰራጫ የማሳውቃችሁ ይሆናል።  

Related posts

I do not serve the government

Kidus Tekleyohannes

A statement from the Joint Task Force on Security and Safety Ethiopia

Kidus Tekleyohannes

After the peace agreement, ” Ethnic cleansing is taking place in western Tigray” Human Rights Watch

Kidus Tekleyohannes

Leave a Comment